100% found this document useful (1 vote)
313 views

FDRETax Appeal Commission Directive

Tax

Uploaded by

yonas
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as PDF, TXT or read online on Scribd
100% found this document useful (1 vote)
313 views

FDRETax Appeal Commission Directive

Tax

Uploaded by

yonas
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as PDF, TXT or read online on Scribd
You are on page 1/ 15

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን መመሪያ


FDRE Tax Appeal Commission
Directive

 Face book address:- FDRE Tax Appeal Commission


(የኢፊዲሪ ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን)
 E/mail address: - taxapp33@ gimal.com

1
የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች

ራዕይ
ፍትሐዊ የግብር ውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት ተፈጥሮ ማየት፡፡

ተልዕኮ
ህግንና አሰራርን መሠረት በማድረግ የህግ የበላይነትንና ልማትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፍትሐዊ፣
ቀልጣፋና ውጤታማ ተደራሽ የሆነ የታክስ ውሳኔዎችን መስጠት፡፡

እሴቶች
 ግልጽነት
 ተደራሽነት
 ነፃነትና
 ተጠያቂነት
 ውጤታማነት
 ፍትሐዊነት
 ገለልተኛነት
 ብቃት

2
የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ሥልጣንና ተግባራት

የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 86 መሠረት በኮሚሽን ደረጃ የተቋቋመ ተቋም ሲሆን
ኮሚሽኑ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 86 መሠረት የሚከተሉት ኃላፊነትና ተግባር ይኖሩታል፡፡ እነዚህም

1) ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሠረት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ይሆናል፡፡


2) በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን መ/ቤት በሚጣሉ የታክስ ውሳኔዎች የታክስ ከፋዩ ህብረተሰብ የሚያቀርባቸው
የታክስ ይግባኝ ቅሬታዎችን/አቤቱታዎችን ይሰማል፣ ይመረምራል፣ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
3) ኮሚሽኑ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ እንዲራዘም የሚቀርብ ማመልከቻ የሚስተናገድበትን ሥነ-ሥርዓት የሚወስን
መመሪያ ያወጣል፣ እንዲተገበር ያደርጋል፡፡
4) ኮሚሽኑ የጽሑፍ ማመልከቻ ሲቀርብለት እና አጥጋቢ ምክንያት መኖሩን ሲያምን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(1) የተመለከተውን የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ሊያራዝም ይችላል፡፡
5) ለዚህ አንቀጽ ዓላማ ማሳኪያ በኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት የፀደቀ የይግባኝ ማመልከቻ ቅጽ ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ
እንዲደረግ ይደርጋል፡፡
6) ኮሚሽኑ በአንቀጽ 89 ንዑስ አንቀጽ (1) (ለ) መሠረት የቀረበው የውሳኔ ምክንያቶች መግለጫ አጥጋቢ ሆኖ
ካላገኘው በጽሑፍ ማስታወቂያ ባለሥልጣኑን በማስታወቂያው በተመለከተው ጊዜ ውስጥ የውሳኔውን
ምክንያቶች የሚያብራራ ተጨማሪ መግለጫ እንዲያቀርብ ሊያዝ ይችላል፡፡
7) ኮሚሽኑ ለይግባኙ አወሳሰን ሌሎች ሠነዶችን ማየት ጠቃሚ ነው ብሎ ሲያምን ባለሥልጣኑን በጽሑፍ
ማስታወቂያ በማስታወቂያው በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ሠነዶች እንዲያቀርብ ሊያዝ ይችላል፡፡
8) ፕሬዝዳንቱ ከኮሚሽኑ ችሎቶች የአንዱ አባል በመሆን ያገለግላል፡፡
9) በይግባኝ የተነሱትን ጭብጦች ግምት ውስጥ በማስገባት እንደ አስፈላጊነቱ ይግባኙን ለመስማት አባላት
ይመድባል፡፡
10) የኮሚሽኑን አሠራር በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጨማሪ መመሪያ ሊወጣ ይችላል፡፡
11) የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 88 መሠረት የሚቀርብን ይግባኝ የክልል የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን
እንዲያይ የውክልና ሥልጣን ሊሰጥ ይችላል፡፡
12) ኮሚሽኑ የቀረበለትን ይግባኝ በአንቀጽ 91 ንዑስ አንቀጽ (5) እና( 7) በተደነገገው መሠረት በመስማት ውሳኔ
ይሰጣል፡፡
13) ኮሚሽኑ የይግባኝ ማመልከቻ ከቀረበለት ቀን ቀጥለው ባሉት 120 (አንድ መቶ ሃያ) ቀናት ውስጥ በቀረበው
ይግባኝ ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
14) ፕሬዝዳንቱ የጉዳዩን ውስብስብነት ከግምት በማስገባት እና ለፍትህ አሰጣጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለተከራካሪ
ወገኖች የጽሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት የይግባኝ መወሰኛ ጊዜውን ከ 60 (ከስልሳ) ቀናት ላልበለጠ ጊዜ
ሊያራዝመው ይችላል፡፡
15) ኮሚሽኑ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) ወይም (3) የተመለከተውን የጊዜ ገደብ ሳያከብር መቅረቱ ኮሚሽኑ
የሰጠውን ውሳኔ ተቀባይነት ሊያሳጣው አይችልም፡፡

3
16) የቀረበው ይግባኝ የታክስ ስሌትን የሚመለከት ከሆነ ኮሚሽኑ፡ በታክስ ስሌቱ የተወሰነውን የገንዘብ መጠን
ሊያፀናው፣ ሊቀንሰው፣ ወይም ስሌቱን በሌላ አኳኋን ሊያሻሽለው፤ ወይም በሚሰጠው መመሪያ መሠረት
እንደገና እንዲመለከተው የታክስ ስሌቱን ለባለሥልጣኑ ሊመልሰው፤ ይችላል፡፡
17) ኮሚሽኑ በታክስ ስሌት ላይ የቀረበን ይግባኝ በመመርመር የታክስ ስሌቱ ሊጨመር ይገባል የሚል እምነት
ሲኖረው፣ ኮሚሽኑ የታክስ ስሌቱን ማስታወቂያ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) (ለ) መሠረት ለባለሥልጣኑ
መልሶ ይልካል፡፡
18) የቀረበው ይግባኝ፣ ይግባኝ የሚባልበትን ሌላ ውሳኔ የሚመለከት ከሆነ ኮሚሽኑ ውሳኔውን ሊያፀናው፣
ሊያሻሽለው ወይም ሊሽረው ወይም ኮሚሽኑ በሚሰጠው መመሪያ እንደገና እንዲመለከተው ለባለሥልጣኑ
መልሶ ሊልከው ይችላል፡፡
19) ኮሚሽኑ የውሳኔውን ግልባጭ ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ
ተከራካሪ ወገን ይሰጣል፡፡
20) ኮሚሽኑ የሚሰጠው ውሳኔ ውሳኔው የተመሠረተባቸውን ምክንያቶች፣ መሠረታዊ በሆኑ የፍሬ ነገር ጉዳዮች
ምርመራ የተገኘውን ውጤት እና ለውሳኔው መሠረት የሆነውን ማስረጃ ወይም ለውሳኔው መሠረት የሆነውን
ሌላ ነገር ማካተት አለበት፡፡
21) ኮሚሽኑ በቀረበለት ይግባኝ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ወይም ኮሚሽኑ በውሳኔ
ማስታወቂያው ከተገለጸው ሌላ ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
22) ኮሚሽኑ ይግባኙን ላቀረበው ታክስ ከፋይ የወሰነለት እንደሆነ፣ ባለሥልጣኑ ይህንን ውሳኔ ለማስፈፀም የተሻሻለ
የታክስ ስሌት ማስታወቂያ መስጠትንም ጨምሮ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (8) መሠረት የውሳኔው
ማስታወቂያ በደረሰው 30 (ሠላሳ) ቀናት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑትን እርምጃዎች ሁሉ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
23) የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት የኮሚሽኑን አስተዳደራዊ ጉዳዮች በኃላፊነት ይመራል፡፡
24) ኮሚሽኑ ሬጅስትራር እና ፕሬዚዳንቱ በሚወስነው መሠረት ሌሎች ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡
25) የኮሚሽኑ ሬጅስትራር ፕሬዚዳንቱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ለተሰጠው ኃላፊነት የፕሬዚዳንቱ ረዳት
በመሆን አስፈላጊ ወይም ተገቢ የሆኑ ተግባራት ያከናውናል እንዲሁም ፕሬዚዳንቱን በመወከል የኮሚሽኑን
አስተዳደራዊ ጉዳዮች ይፈጽማል፡፡
26) የኮሚሽኑ በጀት በመንግሥት የሚመደብ ይሆናል፡፡
27) ኮሚሽኑ የተሟሉ እና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል፡፡
28) የኮሚሽኑ የሂሳብ መዛግብትና ሌሎች የገንዘብ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚወክለው ኦዲተር ኦዲት
ይደረጋሉ፡፡
29) የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ለእያንዳንዱ የበጀት ዓመት የኮሚሽኑን ጉዳዮች የሚመለከት ሪፖርት ያዘጋጃል፡፡
30) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ለበጀት ዓመቱ የተዘጋጀው ሪፖርት የበጀት ዓመቱ ከተጠናቀቀ በኋላ
በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ያቀርባል፡፡

4
የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የአሰራርመመሪያ
መመሪያ ቁጥር 02 /2011
ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽኑ የሚቀርቡ ይግባኞች እናመልሶች ከአቤቱታ አቀራረብ ጀምሮ ውሳኔ እስከሚያገኙበት
ድረስ የሚያልፍበትን ሂደትና የሚከተሉትን ሥርዓት ግልጽ ማድረግ በማስፈለጉ፤

የኮሚሽኑን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ተደራሽ ፍትሐዊ ፈጣን፣ ውጤታማ፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው
እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፤
በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 90(2) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን
መመሪያ አውጥቷል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌዎች
1.አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ‹‹የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የአሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2011››ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2.ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጥ ካልሆነ በስተቀር፡-

1/"ኮሚሽን" ማለት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008አንቀጽ 86 መሰረት የተቋቋመ የታክስ ይግባኝ
ኮሚሽን ነው፤
2/"ፕሬዚዳንት"ማለት በአዋጁ አንቀጽ 86(2) መሠረት የተሾመ የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ነው፤
3/"የኮሚሽኑ አባላት"ማለት በአዋጁ አንቀጽ 87(1)መሰረት የሚሾሙ የኮሚሽኑ ዳኞች ናቸው፤
4/"ሬጂስትራር"ማለት የኮሚሽኑ ሬጂስትራር ነው፤
5/"ውሳኔ"ማለት ኮሚሽኑ በይግባኝ የቀረበለትን ጉዳይ መርምሮ የሚሰጠው ውሳኔ ነው፤
6/"መልስ ሰጪ"ማለት እንደ አግባብነቱ የገቢዎች ሚኒስቴር ወይም የጉምሩክ ኮሚሽን ወይም የነዚሁ ተቋማት
ቅርንጫፍ ነው፤
7/ "ይግባኝ" ማለት በመልስ ሰጭ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለኮሚሽኑ የሚቀርብ ይግባኝ ነው፤
8/"ይግባኝ ባይ"ማለት በመልስ ሰጭ ውሳኔ ላይ ለኮሚሽኑ የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ሰው ነው፤
9/ በታክስ አስተዳደር አዋጅ፣ በገቢ ግብር አዋጅ እና በጉምሩክ አዋጅ ትርጉምየተሰጣቸው ቃላትና ሐረጋት ለዚህ
መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

3.የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ ለኮሚሽኑ በይግባኝ በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ እና ከጉዳዮቹ ጋር በተያያዘ አግባብነት ባላቸው ሰዎች ላይ
ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ክፍል ሁለት
ስለይግባኝ
4. ይግባኝን ስለማቅረብ
5
1/ይግባኝ መቅረብ ያለበት በይግባኝ ባይ ወይም በሕጋዊ ወኪሉ አማካኝነት ብቻ ነው፤
2/ይግባኙ በጽሑፍ ሆኖ በይግባኝ ባይ ወይም በሕጋዊ ወኪሉ ተፈርሞ በአካል ለኮሚሽኑ መቅረብ አለበት፡፡
5.የይግባኝ አቤቱታ ይዘት
1/ለኮሚሽኑ የሚቀርብ ይግባኝ በጽሑፍ ሆኖ ፡-
ሀ/የይግባኝ ባዩን ስምና አድራሻ፣በውክልና ሲሆን በይግባኝ ባይ የተሰጠውንየውክልና ሥልጣንእንዲሁም
የተወካይ ስምና አድራሻ፣
ለ/የታክስ መለያ ቁጥሩን፣
ሐ/ይግባኙ መሠረት ያደረገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች፣ይግባኝ የተመሰረተበት ፍሬ ነገር እና የህግ ጉዳይ ፣
መ/ይግባኝ የቀረበበትን የግብር ውሳኔ የሰጠው አካል ለውሳኔው የሰጠውን ምክንያት እና የይግባኝ ባይ
መቃወሚያ ፣
ሠ/በማስረጃነት የሚቀርቡ ሰነዶች ፣በምስክርነትእንዲቀርቡ የሚፈልጋቸውሰዎች ስምና
አድራሻእናየሚያስረዱለትን ጉዳይ በአጭሩ፣
ረ/ሌሎች ለኮሚሽኑ ውሳኔ አሰጣጥ አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ጉዳዮች ፣
ማካተት አለበት፡፡
2/ ይግባኝ ባይ ለጉዳዩ አግባብነት አላቸው የሚላቸውን ማስረጃዎች ዝርዝርና የሚያስረዱለትን ፍሬ ነገር አጭር
መግለጫ ከማመልከቻው ጋር አያይዞማቅረብ አለበት፡፡

6.ከይግባኝ አቤቱታ ጋር ተያይዘው ስለሚቀርቡ ሰነዶች


1. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5(2) መሰረት ከይግባኝ አቤቱታ ማመልከቻ ጋር ተያይዞ የሚቀርበው የማስረጃ ዝርዝር ፡-
ሀ/ የማስረጃ ዝርዝር መግለጫና በዝርዝሩ የተጠቀሱ ሰነዶችን፤
ለ/የይግባኝ ቅሬታየቀረበበት የአቤቱታ አጣሪ ጽ/ቤት ውሳኔ ወይም ይግባኙ የቀረበውበአዋጁአንቀጽ 55(7)
መሰረት ከሆነ የግብር ውሳኔ ማስታወቂያውን፤
ሐ/ለአቤቱታ አጣሪ የቀረበውን አቤቱታ ግልባጭ፤
መ/ይግባኙን ለማቅረብ በቅድሚያ መከፈል ያለበትን ክፍያ ስለመፈጸሙ የሚያረጋግጥ ሰነድ፤
ሠ/ይግባኙየሚቀርበው በውክልና ከሆነ ውክልና የተሰጠበት ሰነድ፤
ረ/ይግባኝ ባይ የሕግ ሰውነት ያለው ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የመተዳደሪያ ደንብ፤የመመስረቻ
ጽሑፍ፤ያካተተ መሆን አለበት፡፡
2. የይግባኝ አቤቱታዎች በሚቀርቡበት ጊዜ የሚቀርቡ ሰነዶች ከኦሪጅናል ሰነዱ ጋር ለመመሳከሩ በሬጅስትራሩ
መረጋገጥ አለባቸው፡፡
7.የይግባኝአቤቱታ ተቀባይነት
1. በሚከተሉት ሁኔታዎች የይግባኝ አቤቱታው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
ሀ/ይግባኙ የህግም ሆነ የፍሬ ነገር መሠረት የሌለው ከሆነ፤
ለ/ይግባኙ መቅረብ ከሚገባው ጊዜ ዘግይቶ የቀረበ ከሆነ እና ዘግይቶ የሚቀርብ ይግባኝ ተቀባይነት የሚያገኝበትን
ምክንያቶች የማያሟላ ከሆነ፣

6
ሐ/ይግባኝ በተባለበት ጉዳይ መከፈል የሚገባው ቅድመ ክፍያ ያልተከፈለ ከሆነ፣
መ/በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5 እና 6 የተዘረዘሩት ተሟልተው ካልቀረቡ፤
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1(ሐ) እና (መ)መሰረትተቀባይነት ያላገኘ ይግባኝ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ሳያልፍ
ተሟልቶ መቅረብ ይችላል፤

8.የይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነት ስለመወሰን


1/የይግባኙ ፎርም መሟላቱን መርምሮ የሚወስነው ሬጂስትራሩ ይሆናል፤
2/ሬጂስትራሩ በሌለ ጊዜ የኮሚሽኑ ዳኛ ሊወስን ይችላል፤
3/ ሬጂስትራሩ ወይም የኮሚሽኑ ዳኛይግባኙ ተቀባይነት አላገኘምባለ ጊዜ ተቀባይነት ያላገኘበትን ዝርዝር
ምክንያትመግለጽ አለበት፤
4/ይግባኝ ባይ ሬጂስትራሩ ወይም ዳኛው በሰጠው ውሳኔ ያልተስማማ ከሆነ ወዲያውኑ
ለፕሬዚዳንቱቅሬታውንማቅረብ ይችላል፤
5/ፕሬዚዳንቱይግባኙ ተቀባይነት አላገኘምባለ ጊዜ ተቀባይነት ያላገኘበትን ዝርዝር ምክንያት እና በዚህ ምክንያት
የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ሊያልፍ እንደሚችል መግለጽ አለበት፡፡
ክፍል ሶስት
መልስ እና የመልስ መልስ
9.የይግባኝ አቤቱታን ለመልስ ሰጪ ስለመላክ
1/የይግባኝ አቤቱታው ተቀባይነት እንዳገኘኮሚሽኑ ወዲያውኑ የይግባኙን አቤቱታእና ማንኛውንም ተያያዥ ሰነድ
ለመልስ ሰጭ ይልካል፡፡
2/ኮሚሽኑ በሚወስነው ቀንና ቦታ መልስ ሰጪየጽሁፍ መልስ እና ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
3/ መልስ ሰጪ ይግባኝ አቤቱታው መልስ መስጠት እንዲችል ቢያንስ የ15 ቀናት ጊዜ ሊኖረው ይገባል፡፡
4/ይግባኝ ባይ ወይም ሕጋዊ ወኪሉ መልስ በሚሰጥበት ቀን በመገኘት የመልስ ሰጪን መልስ መቀበል አለበት፡፡
5/የግራ ቀኙ ተከራካሪ ወገኖች በጽሁፍ የሚያደርጉትየሰነድ ርክክብ በችሎት ፊት ይከናወናል፡፡
6/ ኮሚሽኑ የሰነድ ርክክብ ልውውጥ እንደጨረሰ ክርክሩ የሚሰማበትን ቀን ሰዓትና ቦታ ወስኖ ለግራ ቀኙ
ያሳውቃል፤ የክርክር ማሰሚያው ቀን ቢያንስ የ15 ቀናት ጊዜ ይኖረዋል፡፡

10.የመልስ መልስ ስለማቅረብ


1/ይግባኝ ባይ የመልስ መልስ አለኝ የሚል ከሆነ በጽሁፍ ማቅረብ ይችላል፡፡
2/ ይግባኝ ባይ የመልስ መልሱን ለማቅረብ ቢያንስ ከ10 ቀናት ያላነሰ ጊዜ ሊኖረው ይገባል፡፡
3/ይግባኝ ባይ የመልስ መልስ በሚሰጥበት ጊዜ በመልስ ሰጪ ለተነሱት ጉዳዮች መልስ ከመስጠት ባለፈ አዲስ
ነገር ማንሳት አይችልም፡፡

11.ክርክርስለማሰማት
1/ማንኛውም ክርክር በግልጽ ችሎት የሚሰማ ይሆናል፡፡
2/ ሆኖም ለፍትህ አሰጣጥ ይረዳ ዘንድ ችሎቱ በክርክር መስማቱ ሂደት ላይ

7
ሀ/የክርክር መሰማት ሂደቱን የሚያውክ ማንኛውንም ሰው፣
ለ/ምስክሮች ምስክርነታቸውን በነፃነት እንዳይሰጡ ያደረገን ሰው፣
ሐ/ለምስክርነት የመጣን ሰው የምስክርነት ተራው እስኪደርስ ድረስ፣
በችሎት እንዳይገኙ ሊያደርግ ይችላል፡፡
12.ይግባኝ ባይ ክርክር ሲሰማ መገኘት ያለበት ስለመሆኑ
1/ይግባኝ ባይ ወይም ወኪሉ በክርክር መስሚያው ቀንመገኘት የሚኖርበት ሲሆን ካልተገኘ ግን ኮሚሽኑ አንድ
ተለዋጭ ቀጠሮ ሊሰጥ ይችላል፡፡
2/በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሰረት በሚሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ ያልቀረበ ይግባኝ ባይ ይግባኙን እንደተወ
ይቆጠራል፡፡
3/ከዚህ በላይ ያለው ድንጋጌ ቢኖርም ይግባኝ ባይ ያልተገኘበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታ ለኮሚሽኑ ካቀረበ
እና፣
ሀ/ያልተገኘው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሆነ፣ እና
ለ/አቤቱታውን ያቀረበው ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥከሆነ፤
ኮሚሽኑ ጉዳዩ እንዲንቀሳቀስ ሊወስን ይችላል፡፡

13.የመልስ ሰጪ መገኘት
1/የመልስ ሰጪ ተወካይ በክርክርመሰማት ሂደት ላይ መገኘት አለበት፡፡
2/የመልስ ሰጪ በክርክር መሰማቱ ላይ ያልተገኘ ከሆነ ኮሚሽኑ አንድ ተለዋጭ ቀጠሮ ሊሰጥ ይችላል፡፡
3/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት በሚሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮመልስ ሰጭ ያልቀረበ ከሆነ በሌለበት
ክርክር መሰማቱ ይቀጥላል፡፡
4/የመልስ ሰጪ ተወካይ በክርክር ሂደት ማስረጃ የማቅረብ፣ የማስረዳት እና በአጠቃላይ የመልስ ሰጪን ክርክር
የሚያሰማ ይሆናል፡፡

14.የይግባኝ ባይ ተወካይ

1/ይግባኝ ባይ በክርክር ጊዜግለሰብ ከሆነ በራሱ ወይም የህግ ሰውነት ካለው በሥራ አስኪያጅ ወይም በነገረ ፈጅ
ወይም ለመከራከርውክልና ባለው የድርጅቱ ሰራተኛ ሊወከል ይችላል፡፡
2/ከላይ ከተመለከቱት ውጪ በክርክር ጊዜ ይግባኝ ባይን መወከል የሚችሉት በህግ መሠረት ውክልና
የተሰጣቸው ጠበቆች ብቻ ናቸው፡፡
15.ማስረጃዎችን ስለመቀበልና ስለመስማት
1/ኮሚሽኑ የሰው ወይም የሰነድ ማስረጃ ይቀበላል፡፡
2/ማንኛውም የሰው ማስረጃ ምስክርነቱን ከመስጠቱ በፊት ቃለ መሐላ እንዲፈጽም ይደረጋል፡፡
3/ኮሚሽኑ ለፍትሐዊ ውሳኔ አሰጣጥ ይጠቅማል ያላቸውን ማስረጃዎች ከውሳኔ በፊት አስቀርቦ ሊመረምር
ይችላል፡፡

8
4/ በተከራካሪ ወገኖች እንዲቀርብ በኮሚሽኑየታዘዘ ማስረጃ በተባለው ጊዜና በታዘዘው መሠረት ካልቀረበ
ኮሚሽኑ ሊያልፈው ይችላል፡፡
16.ኮሚሽኑ ስለሚሰጣቸው ትዕዛዞች
1/ኮሚሽኑ ይግባኙ በሚሰማበት በማንኛውም ጊዜ የሚከተሉትን ትዕዛዞች ሊሰጥ ይችላል፡፡
ሀ/ጥያቄ ሲቀርብ ተጨማሪ ተከራካሪ ወገን ጣልቃ እንዲገባ፣
ለ/የጉዳዩን መሰማት ለተወሰነ ጊዜ እንዲያቆይ፣
ሐ/ተከራካሪ ወገኖች በጉዳዩ ላይ የመተሳሰብ ውጤት እንዲያቀርቡ፣
መ/ተከራካሪ ወገኖች ተስማምተው መሠረታዊ የሚሏቸውን የሂሣብ መዝገቦች ወይም ሰነዶች ለኮሚሽኑ
እንዲያቀርቡ፣

ረ/ለተያዘው ጉዳይ አግባብነት አላቸው የሚባሉ በሌሎች በህግ ሥልጣን ባላቸው አካላት እጅ የሚገኙ ወይም
የተሰጡ ውሳኔዎችን ወይም የተሰጡ የምስክርነት ቃሎች ወዘተ ያሉበትን ቦታ እንዲያመለክቱ ፣
ሰ/ተከራካሪ ወገኖች ለተያዘው ጉዳይ አስፈላጊየሆነ የባለሙያ፣የቴክኒክ ወይም ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዲያቀርቡ፤
ሸ/ፍትሐዊ ውሳኔ ለመስጠት አስፈላጊነው ብሎ ያመነበትን ማንኛውንም የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ
እንዲያቀርብ
2/ኮሚሽኑ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ማንኛውንም ተቋም ሰነድ፣የሰውማስረጃዎች ወይም አስረጂዎች እንዲቀርቡ
ወይም መርምረው ውጤት እንዲገልፁ ሊያዝ ይችላል፡፡
3/ማንኛውም የኮሚሽኑ ትዕዛዝ በጽሁፍ ለተከራካሪ ወገኖች እና ለሚመለከታቸው አካላት መገለጽ አለበት፣
በጽሁፉም ላይ ቦታ እና ሰዓት መገለጽ ያለበት ሲሆን ማንኛውም ሰው ትዕዛዙን ማክበርና መፈጸም ይኖርበታል፡፡
4/ማንኛውም ተከራካሪ ወገን የተሰጠውን ትዕዛዝ አግባብነት የለውም ወይም መሻሻል አለበት ወይም ለተወሰነ ጊዜ
መቆየት አለበት ብሎ ካመነ ለኮሚሽኑ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፣ አቤቱታውም በጽሁፍ የሚቀርብ ሆኖ
ኮፒውምለሌላኛው ወገን ተከራካሪ ከ15 ቀን በፊት መድረስ አለበት፡፡
5/በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 የሚቀርበው የጽሁፍ አቤቱታትዕዛዙየሚቀርበትን፣ የሚሻሻልበትን ወይም
የሚቆይበትን ምክንያት በግልጽ ማካተት አለበት፡፡
6/በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 መሰረት በሚቀርበው የጽሁፍ አቤቱታ ላይ ኮሚሽኑ ብይን ይሰጣል፡፡
7/ማንኛውም ተከራካሪ ወገን በኮሚሽኑ የተሰጠውን ትዕዛዝ ካልፈጸመ ኮሚሽኑ እንደ አግባብነቱ ጉዳዩ እንዲቋረጥ
ወይም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተከራካሪ ወገን በሌለበት ክርክሩ እንዲቀጥል ወይም የተጠቀሰው ማስረጃ
ተቀባይነት እንዳይኖረውሊወሰን ይችላል፡፡

17.የኮሚሽኑ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት


1. እያንዳንዱ ችሎት አምስት አባላት የሚኖሩት ሲሆን ከኮሚሽኑ አባላት ሦስቱ ሲገኙ ችሎቱ የተሟላ ይሆናል፡፡
2. ኮሚሽኑ በቀረቡለት የይግባኝ ጉዳዮች ላይ በድምጽ ብልጫ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
3.ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል፡፡
4. በሃሣብ የተለየ የጉባዔው አባል የሀሳብ ልዩነቱን በውሳኔው ያሰፍራል፡፡

9
ክፍልአራት
ልዩልዩድንጋጌዎች

18. ሌሎች ተፈጻሚነት የሚኖራቸው ህጎች


የታክስአስተዳደር አዋጅ፣የጉምሩክ አዋጅ እና የፍትሐብሔርስነሰርዓት ህግእንደአግባብነታቸው ተፈጻሚነት
ይኖራቸዋል፡፡
19.የተሻሩ አሰራሮችና መመሪያዎች
ይህ መመሪያ ተፈፃሚ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም ከዚህመመሪያጋር የሚቃረን አሰራር ወይም መመሪያ
ተሸሯል፡፡
20.መመሪያው ተፈጻሚ ስለሚሆንበት ጊዜ
ይህ መመሪያ ተፈርሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ-----/---/2011

አብይ አህመድ (ዶ/ር)


የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ሚኒስትር

10
ይግባኝ የማቅረቢያ ጊዜን ስለማራዘም ወይም ዘግይቶ የሚቀርብ የይግባኝ ማመልከቻ
የሚስተናገድበት ስርዓት ለመወሰን የወጣ መመሪያ
መመሪያ ቁጥር 01/2011
በታክስ አስተዳደር አዋጁ ኮሚሽኑ አጥጋቢ ምክንያት መኖሩን ሲያምን የይግባኝ መቅረቢያ ጊዜ ሊያራዝም
እንደሚችል የተደነገገ በመሆኑ ፤
በተለያየ ምክንያት ዘግይቶ የሚቀርብ የይግባኝ ማመልከቻ የሚስተናገድበትን ስርዓት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፣

የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 88(4) በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ይህን መመሪያ
አውጥቷል፡፡
ክፍልአንድ
ጠቅላላድንጋጌዎች
1. አጭርርዕስ
ይህ መመሪያ ‹‹የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ እንዲራዘም ወይም ዘግይቶ የሚቀርብ የይግባኝ ማመልከቻ
የሚስተናገድበት ሥርዓትን ለመወሰን የወጣመመሪያ ቁጥር 01/2011›› ተብሎ ሊጠቀስይ ችላል፡፡
2.ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፡-
1/"ኮሚሽን" ማለት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 86 መሰረት የተቋቋመ የታክስ ይግባኝ
ኮሚሽን ነው፤
2/"ፕሬዚዳንት" ማለት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 86(2) መሠረት የተሾመ የኮሚሽኑ
ፕሬዚዳንት ነው፤
3/"የኮሚሽኑ አባላት" ማለት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 87(1)መሰረት የሚሾሙ
የኮሚሽኑ ዳኞች ናቸው፤
4/"ሬጂስትራር" ማለት የኮሚሽኑ ሬጂስትራር ነው፤
5/"ውሳኔ" ማለት ኮሚሽኑ የቀረበለትን ጉዳይ መርምሮ የሚሰጠው ውሳኔ ነው፤
6/"መልስ ሰጪ" ማለት እንደ አግባብነቱ የገቢዎች ሚኒስቴር ወይም የጉምሩክ ኮሚሽን ወይም የነዚሁ ተቋማት
ቅርንጫፍ ነው፤
7/"ይግባኝ" ማለት በመልስ ሰጭ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለኮሚሽኑ የሚቀርብ ይግባኝ ነው፤
8/"ይግባኝ ባይ" ማለት በመልስ ሰጭ ውሳኔ ላይ የይግባኝ አቤቱታ ለኮሚሽኑ ያቀረበ ሰው ነው፤
9/"ዘግይቶ የቀረበ ይግባኝ" ማለት ይግባኝ ሊቀርብበት በሚገባው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያልቀረበይግባኝነው፡፡
10/ "ይግባኝማቅረቢያጊዜውእንዲራዘምየሚቀርብአቤቱታ"ማለትይግባኝየማለትመብትያለውሰው ይግባኝ
የሚያቀርብበት ጊዜ ከማለፉ በፊት ይግባኝ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው የሚቀርብ አቤቱታ ነው፡፡
11/ በታክስ አስተዳደር አዋጅ፣ በጉምሩክ አዋጅ እና በገቢ ግብር አዋጅ ትርጉም የተሰጣቸው ቃላትና ሐረጋት ለዚህ
መመሪያም ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

3. የተፈፃሚነት ወሰን

11
ይህ መመሪያ ለኮሚሽኑ ዘግይተው በሚቀርቡ ወይም ይግባኝ የማቅረቢያ ጊዜያቸው እንዲራዘም በሚጠየቁ
ይግባኞች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ክፍል ሁለት
የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜን ስለማራዘም እና ዘግይቶ ስለሚቀርብ ይግባኝ

4. የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ እንዲራዘም ስለሚቀርብበት ማመልከቻ


1/ይግባኝ ባይ ወይም ወኪሉ የይግባኝ ማቅረቢያው ጊዜ ከማለፉበፊት ይግባኝ የማቅረቢያ ጊዜው እንዲራዘምለት
በጽሁፍ ለኮሚሽኑ ሊያመለክት ይችላል፤
2/ይግባኝ ባይ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ እንዲራዘም ለትጥያቄውን ሲያቀርብ ምክንያታዊያ ለሆነ መዘግየት
ያለመኖሩን እና እንዲራዘም የፈለገበትን ምክንያት በማመልከቻው መግለጽእና ማስረጃዎች ማቅረብ አለበት፤

5. የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜን ስለማራዘም


ኮሚሽኑ በአንቀጽ 4 መሰረት የቀረበውን ማመልከቻ በመመርምር ይግባኝ ባዩ ይግባኙን ያላቀረበው ከአቅም በላይ
ወይም አሳማኝ በሆነ ምክንያት መሆኑን ሲያምንበት የይግባኝ ማቅረቢያውን ጊዜ የይግባኝ ማቅረቢያው ቀን
ካበቃበት ቀን ጀምሮ ከ15 ቀን ላልበለጠ ጊዜ ሊያራዝምለት ይችላል፡፡

6. ዘግይቶ ስለሚቀርብ ይግባኝ


1/ዘግይቶ ለሚቀርብ ይግባኝ በቅድሚያ የዘገየ ይግባኝ ይከፈትልኝ አቤቱታ ማቅረብ አለበት፡፡
2/በአቤቱታው ይግባኙ በጊዜው ሊቀርብ ያልቻለበትን ምክንያት እና አሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች በዝርዝር
ማቅረብ አለበት፡፡

7. ዘግይቶ የቀረበ ይግባኝ የሚስተናገድበት ስነ ሰርዓት


1/ኮሚሽኑ አቤቱታው በደረሰው በሶስት ቀናት ውስጥ መልስ ሰጭ በአቤቱታው ላይ አስተያየት እንዲሰጥ
ይልክለታል፡፡
2/ የመልስ ሰጭ አስተያየት የሚሰጥ ከሆነ በጽሑፍ ማቅረብ አለበት፤
3/ የመልስ ሰጪው አስተያየት ከሰጠ በኋላ ወይም አስተያየቱን በተወሰነው ቀን ካላቀረበ ኮሚሽኑ በቀረበው አቤቱታ
ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
4/ ዘግይቶ የቀረበን ይግባኝ ተቀባይነት ለመወሰን ኮሚሽኑ በችሎት ክርክሩን ሊሰማ ይችላል፡፡

8. ዘግይቶ የሚቀርብ ይግባኝን ስለመፍቀድ


1/ ኮሚሽኑ በአቤቱታው ላይ የተገለጸው ምክንያት በፍትሐብሄር ህግ አንቀጽ 1793 ላይ ከአቅም በላይ የሆነ
ምክንያት ተብሎ የተገለጸውን ሁኔታዎች ያሟላ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ለተመለከቱት ምክንያቶች በቂና አሳማኝ ማስረጃ አግባብ ካለው አካል መቅረብ
አለበት፡፡
3/ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠ ኮሚሽኑ ይግባኙ እንዲቀርብ ውሳኔ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ በ10
(አስር) ቀናት ውስጥ ይግባኙን እንዲያቀርብ ይፈቀድለታል፡፡

12
4/ይግባኙ ተቀባይነት የለውም ተብሎ በኮሚሽኑ በወሰነ ጊዜ ውሳኔው ላይ ይግባኝ ባዩ እና ለመልስ ሰጭ በጽሑፍ
እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡

10. ተፈፃሚነት የማይኖራቸው አሰራሮች


ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም አሰራር ወይም መመሪያ
ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
11. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ ተፈርሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ.ም

ሙሉጌታ አያሌው

የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት

13
የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን
የይግባኝ ማመልከቻ ቅጽ
የይግባኝ ባይ/ ተወካይ ስም ---------------------------------

አድራሻ----------------------------------

ይግባኝ የቀረበበት ቀን -----------------------------------

ይግባኝ የቀረበበት የግብር አይነት-----------------------

ይግባኝ የቀረበበት የግብር ዘመን -----------------------

የታክስ መለያ ቁጥር ---------------------------------------

 ኮምሽኑ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 56 እና 88 ወይም በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር
859/2006 አንቀፅ 155 መሰረት ጉዳዩን የማየት ስልጣን አለው ፣
 የይግባኝ ባይ በፍታብሔር ስነ ስርዓት ሕግ አንቀፅ 33 መሰረት የመከራከር መብት አለው ፣
 ይግባኙ በህጉ መሰረት በ30 ቀን ቅስጥ የቀረበ ነው፣
 የይግባኝ ባይ ህጉ በሚያዘው መሰረት ማስያዣ ከፍሎ ማስረጃ አያይዟል፣
 የይግባኝ ባይ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የሰጠውን ውሳኔ አያይዟል፣
 ይግባኝ ባይ መጥሪያ ሊያደርስ ይችላል፣

የይግባኝ ባይ የፍሬ ነገር እና የሕግ ክርክር ………...........................................................


...............................................................................................................................
...............................................................................................................................
...............................................................................................................................
...............................................................................................................................
………………….፡፡
ይግባኝ ባይ የሚጠይቀው ዳኝነት ……….....................................................................
...............................................................................................................................
...............................................................................................................................
………………….፡፡
የቀረበው ይግባኝ በፍታብሔር ስነ ስርዓት ሕግ አንቀፅ 92 መሰረት እውነት መሆኑን አረጋግጣለሁ፡፡

14
ይግባኝ ባይ/ተወካይ/ ስም…………………. ፊርማ ………………………………

የማስረጃ ዝርዝር
ሀ/ የሰነድ ማስረጃ
1.
2.
3.

የሚያስረዱት ጉዳይ ባጭሩ፡- ………...................................................................................

...............................................................................................................................
...............................................................................................................................
………………….፡፡

ለ/ የሰው ማስረጃ

ስም አድራሻ

1.
2.
3.

የሚያስረዳው ጉዳይ ባጭሩ ………………….....................................................................

...............................................................................................................................

.................................................፡፡

የቀረበው ይግባኝ በፍታብሔር ስነ ስርዓት ሕግ አንቀፅ 92 መሰረት እውነት መሆኑን አረጋግጣለሁ፡፡

ይግባኝ ባይ/ተወካይ/ ስም………………….


ፊርማ ………………………………

15

You might also like